
Breaking News
ሰበር ዜና፦ ሱዳን ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧ አስታወቀች።
ከሱዳን ደህንነት እና መከላከያ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
- መላው አለም በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና በአካባቢው ወኪሉ በአሸባሪው እና በአመፀኛው የፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ሚሊሻ እና በፖለቲካ ደጋፊው በኩል በሱዳን ሉዓላዊነት ፣የግዛት አንድነት እና የዜጎች ደህንነት ላይ የሚፈጸመውን ወረራ ወንጀል ከሁለት አመት በላይ ሲከታተል ቆይቷል።
- የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በአገር ውስጥ ወኪሎቻቸው መሸነፋቸውን ባረጋገጡ ጊዜ በኛ ታጣቂ ሃይሎች የተሸነፈው ሐይል የላቀ ስልታዊ የጦር መሳሪያ ለማቅረብ ጥረት አድርጓል።
- በአገሪቷ በሚገኙ ወሳኝና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃቶች የተፈፀመ ሲህን ከእነዚህም መካከል የነዳጅ ዘይትና ጋዝ ዴፖዎች፣ ፖርት ሱዳን ወደብና አውሮፕላን ማረፊያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችና ሆቴሎች ኢላማ በማድረግ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ሕይወትና ንብረት አደጋ ላይ መውደቁ የቀጠናውንና የዓለም አቀፍ ደህንነትን በተለይም የቀይ ባህርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ጉዳይ ነው።
- በዚህ እየተካሄደ ባለው ወረራ ምክንያት የደህንነት እና የመከላከያ ምክር ቤት የሚከተለውን ወስኗል።
- የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሱዳን ህዝቦች ጠላት መሆኗ አውጇል።
- ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ማቋረጥ፤
- የሱዳን ኤምባሲ እና ቆንስላ ጄኔራል በኢሚሬትስ እንዲዘጋ፤



